“መንሹ በእጁ ነው፤ ...... "
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! “መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውን ያጠራዋል” ማቴ 3:12 በምህረቱ ባለጠጋ የሆነ ጌታ እግዚአብሔር የመጨረሻውን ፍርዱን ከመግለጡ በፊት የንስሐ ዕድል መስጠት ልማዱ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ከኖኅና ከሰዶም ሰዎች ገጠመኝ ከነነዌም ታሪክ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ የተመለሱ ድነዋል፤ በልባቸው ጥንካሬ ጸንተው በክፋት የቀጠሉ ጠፍተዋል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ከላይ የተጠቀሱትን ታሪኮች እንደማሳያ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ የሰማው የለም እንጂ፡፡ ማቴ 12፡41፤ ማቴ 24፡38፤ ሉቃ 17፡28-32 አውድማውን ያጠራ ዘንድ መንሹን የያዘው ከመገለጡ በፊት ቤተ አይሁድ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ሄደው ነበር፡፡ ዕለት ተዕለት ጌታ እግዚአብሔርን በከንፈራቸው ምህረትንና በረከትን በሥራቸው ግን ፍርድንና ጥፋትን እየለመኑት ነበር፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው እርሱ ግን አባቱን በግፍ ያስገደሉበትን ብላቴና ለበቀል ሳይሆን ወደ ምህረት ጮኾ እንዲጠራቸው ላከው፡፡ በምድረ በዳ (አበው በትርጓሜ ምድረ በዳ የተባለ የአይሁድ ልቡን ነው፡፡ ምድረ በዳ ውሃ ልምላሜ እንደሌለበት የአይሁድ ልቡናም ከሃይማኖት ከምግባር የተራቆተ ነበር ይላሉ፡፡ ስም፣ ሥርዓትና ምልክት ብቻ ቀርቶላቸው ነበር፡፡ ዛሬም በእኛ ዘንድ ያለው ክርስትና ስም፣ ሥርዓትና ምልክት ብቻ ቀርቶልን በፍቅር…
Read more...