Login
Main menu

መልእክቶች

“መንሹ በእጁ ነው፤ ...... "

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! “መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውን ያጠራዋል” ማቴ 3:12 በምህረቱ ባለጠጋ የሆነ ጌታ እግዚአብሔር የመጨረሻውን ፍርዱን ከመግለጡ በፊት የንስሐ ዕድል መስጠት ልማዱ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ከኖኅና ከሰዶም ሰዎች ገጠመኝ ከነነዌም ታሪክ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ የተመለሱ ድነዋል፤ በልባቸው ጥንካሬ ጸንተው በክፋት የቀጠሉ ጠፍተዋል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ከላይ የተጠቀሱትን ታሪኮች እንደማሳያ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ የሰማው የለም እንጂ፡፡ ማቴ 12፡41፤ ማቴ 24፡38፤ ሉቃ 17፡28-32 አውድማውን ያጠራ ዘንድ መንሹን የያዘው ከመገለጡ በፊት ቤተ አይሁድ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ሄደው ነበር፡፡ ዕለት ተዕለት ጌታ እግዚአብሔርን በከንፈራቸው ምህረትንና በረከትን በሥራቸው ግን ፍርድንና ጥፋትን እየለመኑት ነበር፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው እርሱ ግን አባቱን በግፍ ያስገደሉበትን ብላቴና ለበቀል ሳይሆን ወደ ምህረት ጮኾ እንዲጠራቸው ላከው፡፡ በምድረ በዳ (አበው በትርጓሜ ምድረ በዳ የተባለ የአይሁድ ልቡን ነው፡፡ ምድረ በዳ ውሃ ልምላሜ እንደሌለበት የአይሁድ ልቡናም ከሃይማኖት ከምግባር የተራቆተ ነበር ይላሉ፡፡ ስም፣ ሥርዓትና ምልክት ብቻ ቀርቶላቸው ነበር፡፡ ዛሬም በእኛ ዘንድ ያለው ክርስትና ስም፣ ሥርዓትና ምልክት ብቻ ቀርቶልን በፍቅር…
Read more...

የ “at least” ክርስትና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! የ “at least” ክርስትና በቅርብ በቅዱስ ጋብቻ አንድ የሆኑ ጥንዶች ስለ ክርስትና ሕይወት ለመወያየት ፈልገው በቢሮዬ ተገናኘን፡፡ ውይይታችን ከተነሱት በርካታ ጉዳዮች የዘመኑን የክርስትና ሕይወት አጉልቶ የሚያሳዩ ሁለት ነጥቦችን እነሆ፡፡ የመጀመሪያው ከእንግዶቹ የተነሳው ሀሳብ በምንኖርበት አገር የሚያስተምሩን ካህን በክርስትና ሕይወት ስንኖር “at least” እነዚህ እነዚህ ነገሮችን ልንፈጽም እንደሚገባ ነግረውናል፤ እርስዎስ ምን ይመክሩናል? በሚል ውይይታችንን ጀመርን፡፡ በተቀመጥኩበት የጌታ እግዚአብሔር ፈቃዱ የተገለጠበትን መጽሐፍ ቅዱስን በኅሊናዬ ለመዳሰስ ሞከርኩ፡፡ እናም ላገኘው ያልቻልኩት ነገር ቢኖር “at least” በሚል ቀዳሚ ቅጽል የተቀመጠን ትዕዛዝ ነው፡፡ መንግስተ እግዚአብሔርን ለመውረስ የተቀመጠ “minimum requirement” ምን እንደሆነ ማወቅ ብችል ብዬ አሁንም ለማሰብ ሞከርኩ ግን አሁንም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም ያ መስፈርት መንግሰቱን ለመውረስ ካበቃ “minimum requirement” ሊሆን አይችልም፡ ፡ ነገር ግን በተለምዶ መምህራነ ወንጌል ክርስቲያኖች ከሆንን “at least” ይህን ልንፈጽም ይገባናል እያልን ስለምናስተምር፤ አበ ነፍሳትም ልጆቻችንን ስንመክር ልጆቼ “ቢያንስ” ይህንና ይህን ለማድረግ ሞክሩ ስለምንል ምዕመኑን የ “at least” ክርስትና ውስጥ አመቻቸነው፡፡ ምዕመኑም ለሚበልጠው ጸጋ…
Read more...

እስረኞቹ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን! በተኛበት የዋሻ እስር ቤት ቅዝቃዜ ሰውነቱ ደንዝዟል ለእርሱ ብቻ በሚሰማው ቃል ግን መንፈሱ ግሏል፡፡ አካሉ በደረሰበት እንግልት ደቋል ልቡ ግን እንደ ዓለት ፀንቷል፡፡ የመንፈስ ልጆቹ ዓይን ውስጥ ያየው አንተ ከሌለህ ምን እንሆናለን? የሚለው ጭንቀት የማያንቀላፋ እረኛ የራሳቸውን ፀጉር እንኳ ቆጥሮ የሚያውቅ ጠባቂ እንዳላቸው ካለመረዳት የመጣ እንደሆነ በመረዳቱ የፀናውን እውነት እንደሚገባው አልገለጥኩላቸው ይሆን? ሲል ላፍታ አሰበ፡፡ ከተቀመጠበት በውኃ የላቆጠ የእስር ቤት ወለል ላይ ተነስቶ የእስር ቤቱን ዘብ ለልጆቹ መልዕክት የሚጽፍበት ብዕርና ክርታስ እንዲሰጠው በትኁት ድምጽ ለመነው፡፡ በጭካኔ የደደረው የሮማ ወታደር ልብ በማያውቀው ምክንያት በእስረኛው ላይ መጨከን ተሳነው፡፡ ትንሽ እልፍ ብሎ ከተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ ብዕርና ክርታሱን እንዲሁም ቁራሽ ዳቦ አቀበለው፡፡ ኅብስቱን እንደ ተቀበለ እጆቹ እየተንቀጠቀጡ እንባ ባቀረሩ ዓይኖቹ ዘቡን ተመለከተው፡፡ ዘቡ ምን የሚያስከፋ ነገር እንዳደረገ በመደናገር ትኩር ብሎ እስረኛውን ሲያጠናው በዕድሜና በእንግልት ከደከመ ልሳን የሚያስደንቅ ጥንካሬ ያለው ቃል መፍለቅ ጀመረ፡፡ እኛ አስራ ሁለታችን፣ እናቱና ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት ሴቶች አብረን አጠገቡ ጉብታው ላይ ተቀምጠናል ሕዝቡ…
Read more...

መሻገር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! የጳጉሜን ወር ከኖርንበት ለመኖር ተስፋ ወደ ምናደርግበት፤ ከሸኘነው ያለፈ ዓመት ወደ ምንቀበለው አዲስ ዓመት መሻገሪያ ናት፡፡ በባህላችንም በአዲስ ዓመት መባቻ ስንገናኝ የምንለዋወጠው መልካም ቃል ‹‹እንኳንከዘመንዘመንአሸጋገረን›› የሚል ነው ለመሆኑ ከዘመን ወደ ዘመን መሻገር ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሰው ወደ አዲስ ዘመን ተሻገረ የምንለው እንዴት ነው? ወይስ ከዘመን ዘመን መሻገር ማለት ለዘመናት መቁጠሪያነት ጌታ እግዚአብሔር በጠፈር ላይ ያኖራቸውን ዐውደ ፀሐይ፣ ዐውደ ወርኅ እና ዐውደ ከዋክብት ተጠቅመን የቀመርነውን የቀን አቆጣጠር አንድ ዐውድ ጨርሰን ሌላውን መጀመር ነው? ጌታ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በጊዜ እየሠፈረ የፈጠረበት ምክንያት ፊት ያልነበሩ ኋላም ኃላፊ መሆናቸውን ሲያመለክተን ነው፡፡ ፍጥረታትን የሚሰፍር ጊዜ ባይኖር ኖሮ ሁሉ በቅድምና ነበረ ኋላም አያልፍም ለማለት የተመቸ ይሆን ነበር፡፡ ስለሆነም ፍጥረት መለወጥ ማርጀት እንዳለበት ለማጠየቅ ይህን ሂደት የሚሰፍርና የሚያሳውቅ መለኪያ ተሠራለት፡፡ በተጨማሪም ፍጥረታት በጊዜ ውስጥ መገኘታቸው፣ መኖራቸውና ኋላም ማለፋቸው ሠራዒ መጋቢ እንዳላቸው በማመልከት ፍጥረት ሀለወተ እግዚአብሔርን ጮኾ እንዲመሠክር ያስገድዳል፡፡ ሥሉስ ቅዱስ ግን በባህርያቸው ውላጤ በዘመናቸው ብልየት የለበትምና ጊዜ…
Read more...

ፍና ቅዱሳን

መጽሐፉን ለማግኝት +251 923976850 +251 911249756 ከመጽሐፉ የተወሰደ ‹‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፤ የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው ፡፡ ዕብ. 13÷7 The paradise ወይም The Garden of the Fathers በሚለው ታላቅ መጽሐፍ፤ የእስክንድርያው ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፤ የሄሊያ ፓሊስ ሊቀ ጳጳስ ጳላድዮስና ቅዱስ ጄሮም፤ ዘመናቸው ታላቅ የቅድስና ሕይወትን በመምራት ይታወቁ የነበሩ አበውን በአካል በማግኘትና፤ በአካል ለማግኘት ያልቻሉትንም ከደቀ መዛሙርቶቻቸው በመጠየቅ የተጋድሎ ሕይወታቸውንና ድንቅ የሆኑ ምክሮቻቸውን መዝግበው ትተውልናል፡፡ በአባቶች ዘንድ የቅድስናን ሕይወት ለመኖር የነበረን ቁርጠኝነት፤ ለወጣንያን የሥጋ ፈቃድን መቆጣጠርና የቅድስናን ሕይወት መለማመድን የሚያሳዩበት መንገድ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ለቃኘው ኅሊና እጅግ መሳጭ ነው፡፡ ሰውነቱን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ለሚመኝ ሁሉ የቅዱሳንን ሕይወት ከማንበብ የሚበልጥ ነገር አይገኝም፡፡ የንስሐቸው ጥልቀት ልብን ይሰብራል፤ የተጋድሏቸው ትዕግሥት ከዓለት ይልቅ ይጸናል፤ ምክርና ተግሣፃቸው የልብን ሸለፈት ለመግረዝ ከባልጩት ይልቅ ይሰላል፤ ለጌታ እግዚአብሔርና ለሰው ልጅ ያላቸው ፍቅር ዕንባን በዓይን ይሞላል፤ ትኅትናቸው በትዕቢት ያበጠ ኅሊናን ያፈርሳል፤ ጸሎታቸው እንደ በረሃ የደረቀ ሰውነትን ያረሰርሳል፡፡ እምነታቸው ሕሙማነ ሥጋ ወነፍስን ለመፈወስ፤ የዲያብሎስንም ወጥመድ…
Read more...

በአዲስ ዓመት መልካም አዲስ ሕይወት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ይህንን መልዕክት ከማንበቦ በፊት ‹‹ በዚህች ዓመት ደግሞ ተዋት›› በሚል የተጻፈውን መልዕክት ያነቡት ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡ ‹‹ነገ እንደ ዛሬው ወደ አንተ እመጣለሁና ተዘጋጅ››
Read more...

በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ብርታትና ድካም፣ ማግኘትና ማጣት፣ስኬትና ውደቀት፣ ሰላምና ሁከት፣ ጤናና ህመም ሲፈራረቁብን ከረምን፡፡ የመጡትን በመቀበል ደስታና እንደየ ሥራቸው የተጠበቀላቸውን ለመቀበል በሞት ወደ ጌታ የሄዱትን በመሸኘት በሀዘን ስሜታችን ሲቆስልና ሲፈወስ ሲያር እና ሲታደስ ባጅተን አዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ ላደረሰን አምላካችን ሸክላ ሕይወታችን ጥላ መሆኑን ዘንግተን ዛሬም እንደ አምና አዲሱን ዓመት በአሮጌ መንፈስ ለመቀበል ለተቃረብን ሁሉ የጌታ መንፈስ ቅዱስ መልዕክት እነሆ፡፡ ‹‹በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት›› ሉቃ 13፡6-9 በአንድ ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በማስተማር ላይ ሳለ ጲላጦስ በመሠዊያው ላይ በሰይፉ አርዶ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለደባለቀው ሰዎች ዘግናኝ ፍጻሜ ሊነግሩት ጀመሩ፡፡ ጌታችንም መልሶ እነዚህ ሰዎችና በሰሊሆም ግንቡ ተንዶባቸው የሞቱ ሰዎች ሁሉ ከእናንተ ይልቅ ኃጢአት የሠሩ ይመስላችኋል፤ ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ በማለት አስጠንቅቋል፡፡ ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታም ሆነ አሰቃቂ በሆኑ ሰው ሠራሽ አደጋዎች ብዙ ሰዎችን ከኋላችን ትተን ጽድቅና ኃጢአት ከሚፈራረቁበት መሬት ሥር ቀብረን እኛ ቆመናል ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ነገርግን አዚህ የመደረሳችን ምስጢር እኛ ከእነርሱ ተሽለን መገኘታችን ይሆን? ጌታችን ለጥቆ በወይኑ…
Read more...
Subscribe to this RSS feed

ጠቃሚ አድራሻዎች

መጻሕፍት ቢያነቧቸው

  • * ​ፍቅር 
  • ፍና ቅዱሳን
  • * የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ 
  • * ዝጎራ